1 - Al-Faatiha ()

|

(1) 1. በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)::

(2) 2. ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው።

(3) 3. እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው::

(4) 4. የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው (ለአላህ ብቻ ይገባው)::

(5) 5. (ሙስሊሞች ሆይ! ጌታችሁን) አንተን ብቻ እንገዛለን:: ካንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉ)

(6) 6. ቀጥተኛውን መንገድ ምራን::

(7) 7. የእነዚያን ለእነርሱ በጎ የዋልክላቸውን፤ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)::