90 - Al-Balad ()

|

(1) 1. በዚህ ሀገር (በመካ) እምላለሁ

(2) 2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትሆን።

(3) 3.በወላጂና በወለዳቸውም (በአደምና በዘሮቹ) ሁሉ (እምላለሁ)

(4) 4. ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው::

(5) 5. በእርሱ ላይ አንድም አካል የማይችል መሆኑን ይጠረጥራልን?

(6) 6. "ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ" ይላል፤

(7) 7. አንድም ያላየው መሆኑን ያስባልን?

(8) 8. ለእርሱ ሁለት አይኖችን አላደረግንለትንምን?

(9) 9. አንድ ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፤

(10) 10.ሁለትን መንገዶችስ አልመራነዉምን?

(11) 11.ዐቀበቱን አልወጣም።

(12) 12.ዐቀበቱን መውጣት ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

(13) 13.ያ ጫንቃን መልቀቅ ነው። {1}
{1} ባሪያን ነጻ ማውጣት ማለት ነው

(14) 14. ወይም የረሀብ ባለቤት በሆነ ቀን (ረሀብተኛን) ማብላት፤

(15) 15. የዝምድና ባለቤት የሆነን የቲም፤

(16) 16.ወይም የአፈር ባለቤት የሆነን (ችግረኛ) ማብላት ነው።

(17) 17.ከዚያም ከእነዚያ በአላህ ካመኑትና በመታገስ ላይ አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው።

(18) 18. እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው።

(19) 19. እነዚያ በአናቅጻችን የካዱ ሁሉ እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው።

(20) 20. ለእነርሱ የምትዘጋባቸው እሳትም አለች።