83 - Al-Mutaffifin ()

|

(1) 1. ለቀሻቢዎች ወዮላቸው፤

(2) 2. ለእነዚያ ከሰዎች ለመግዛት ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤

(3) 3. እነርሱም (ለሰዎች) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎሉ (ለሆኑት)::

(4) 4. እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን (በትክክል) አያውቁምን?

(5) 5. ለታላቁ ቀን፤

(6) 6. ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸውን)::

(7) 7. በእውነት የከሓዲያን መዝገብ በእርግጥ በ"ሲጂን" ውስጥ ነው።

(8) 8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ሲጂን" ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

(9) 9. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

(10) 10. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።

(11) 11. ለእነዚያ በፍርድ ቀን ለሚያስተባብሉት::

(12) 12. በእርሱም ወሰን አላፊ ኃጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም::

(13) 13. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ እኒህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል::

(14) 14. ይከልከሉ፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሰሩት የነበሩት ኃጢአት ደገደገባቸው::

(15) 15. ይከልከሉ:: እነርሱ በዚያ ቀን ጌታቸውን ከማየት ተጋራጆች ናቸው::

(16) 16. ከዚያ እነርሱ በእርግጥ ገሀነም ገቢዎች ናቸው::

(17) 17. ከዚያ ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው ይባላሉ::

(18) 18. የ(እውነተኞቹ) ደጋጎች መጽሐፍ በ"ዒሊዩን" ውስጥ ነው።

(19) 19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ዒሊዩን"ም ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

(20) 20. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

(21) 21. (የአላህ) ባለሟሎቹ ይጠብቁታል (ይጣዱታል)

(22) 22. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

(23) 23. በተዋቡ ዙፋኖች ላይ የተደገፉ ሆነው ይመለከታሉ።

(24) 24. ከፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ትረዳለህ (ታውቃለህ)

(25) 25. ተጣርቶ ከታተመ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ::

(26) 26. መደምደሚያው ሚስክ ከሆነ (መጠጥ ይጠጣሉ)። ተሽቀዳዳሚዎች በዚህ ይሽቀዳደሙ።

(27) 27. መበረዣዉም ከተስኒም ነው።

(28) 28. (የአላህ) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት።

(29) 29. እነዚያ (በአላህ ላይ) ያመጹት በእነዚያ (በአላህ) ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበር።

(30) 30. በእነርሱም አጠገብ ባለፉ ጊዜ ይጠቋቆሙባቸው (ይጠቃቀሱባቸው) ነበር::

(31) 31. ወደ ቤተሰቦቻቸዉም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር።

(32) 32. ባዩዋቸዉም ጊዜ፡- "እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው።" ይሉ ነበር።

(33) 33. በእነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲሆኑ::

(34) 34. ዛሬ (በትንሳኤ ቀን) ግን እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑት ሰዎች በከሓዲያን ላይ ይስቃሉ::

(35) 35. በተዋበ ዙፋን ላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆኑ (ይስቃሉ)

(36) 36. ከሓዲያን ይሰሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)::