82 - Al-Infitaar ()

|

(1) 1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤

(2) 2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤

(3) 3. ባህሮችም በተከፈቱና በተደባለቁ ጊዜ፤

(4) 4. መቃብሮችም በተገለባበጡና ሙታን በተነሱ ጊዜ፤

(5) 5. (ያኔ) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያዘገየችውን ታውቃለች።

(6) 6. አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?

(7) 7. በዚያ በፈጠረህ፤ አካለ ሙሉም ባደረገህ፤ ባስተካከለህም፤

(8) 8. በማንኛውም (እርሱ) በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ ጌታህ ምን አታለለህ?

(9) 9 (ሰዎች ሆይ!) ተከልከሉ፤ በእውነት በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ።

(10) 10. በእናንተ ላይ ጠባቂዎች ያሉባችሁ ስትሆኑ፤

(11) 11. የተከበሩ ጸሐፊዎች የሆኑ (ተጠባባቂዎች)

(12) 12. የምትሰሩትን (ሁሉ) ያውቃሉ፤

(13) 13. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

(14) 14.ከሓዲያንም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው::

(15) 15.በፍርዱ ቀን ይገቧታል::

(16) 16.እነርሱም (ምን ጊዜም) ከእርሷ ራቂዎች አይደሉም::

(17) 17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

(18) 18. ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቅህ?

(19) 19. (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን ነው:: ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው::