70 - Al-Ma'aarij ()

|

(1) 1. ወዳቂ (ተከሳች) ከሆነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ::

(2) 2. ከሓዲያን ላይ (ወዳቂ ከሆነው) ለእርሱ መላሽ የለዉም።

(3) 3. የ (ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለዉም)::

(4) 4. መላዕክትና መንፈሱም ልኩ ሀምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ (ይወጣሉ)::

(5) 5. መልካምን ትዕግስት ታገስ::

(6) 6. እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገው ያዩታል::

(7) 7. እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋለን::

(8) 8. ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤

(9) 9. ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ንፋስ) እንደበተነውና እንደሚያበረው በሚሆኑበት ቀን፤

(10) 10. ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን መላሽ የለዉም::

(11) 11. (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል::

(12) 12. በሚስቱም በወንድሙም፤

(13) 13. በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤

(14) 14. በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል)::

(15) 15. ይተው፤እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት።

(16) 16. የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤

(17) 17. (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች::

(18) 18. ገንዘብን የሰበሰበንና ዘካውን ሳይሰጥ የቆጠረንም (ትጠራለች)::

(19) 19. ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ::

(20) 20. ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤

(21) 21. መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ::

(22) 22. ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ::

(23) 23. እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት::

(24) 24. እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤

(25) 25. ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)

(26) 26. እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት የሚያረጋግጡ::

(27) 27. እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት::

(28) 28. የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና።

(29) 29. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤

(30) 30. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር:: እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና::

(31) 31. ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።

(32) 32. እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት::

(33) 33. እነዚያም እነርሱ በምስክሮቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት::

(34) 34. እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት::

(35) 35. እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው::

(36) 36. እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?

(37) 37. ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤

(38) 38. ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?

(39) 39. ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍተወት ጠብታ) ፈጠርናቸው::

(40) 40. (እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን::

(41) 41. ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::

(42) 42. ያንንም የሚሰፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተዋቸው፤ በአሉባልታዎችም ዉስጥ ይዋኙ፤ ይጫወቱም።

(43) 43. ያ ቀን ወደ ጣዖት እንደሚሽቀዳደሙ ሆነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን ነው::

(44) 44. ዓይኖቻቸው ያፈሩ ሆነው፤ ውርደት ትሸፍናቸዋለች:: ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቀን ነው::