(1) 1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በምርመራው ቀን የሚያስተባብለውን ሰው አየህን? (አወከውን?)
(2) 2. ይሀውም ያ የቲምን በኃይል የሚገፈትረው፤
(3) 3. ድሃን በማብላት ላይም የማያነሳሳው ነው።
(4) 4. ወዮላቸው ለሰጋጆች፤
(5) 5. ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት (ሰጋጆች)፤
(6) 6. ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለሆኑት፤
(7) 7. የዕቃ ትውስትንም ሰዎችን የሚከለክሉ ለሆኑት ሁሉ ወዮላቸው::