(1) በረፋዱም፤ (እምላለሁ)
(2) 2. በሌሊትም ጸጥ ባለ ጊዜ እምላለሁ::
(3) 3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም::
(4) የመጨረሻይቱ ዓለም ከመጀመሪያይቱም ይልቅ ላንተ በላጭ ናት::
(5) ጌታህም ወደ ፊት ብዙ ስጦታ በእርግጥ ይሰጥሃል። ትደሰታለህም።
(6) 6. የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)::
(7) 7. የሳትክም ሆነህ አገኘህና መራህ::
(8) 8. ደሃም ሆነህ አገኘህና አከበረህ::
(9) 9. እናም የቲምን አትጨቁን::
(10) 10. ለማኝንም አትገላምጥ::
(11) 11. የጌታህንም ጸጋ ግለጽ::