(1) 1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ! {1}
{1} ይህ አንቀጽና ቀጥሎ ያሉት ከቁርአን መጀመሪያ የወረዱ አንቀጾች ናቸው። በኑር ተራራ ላይ በምገኘው የሂራእ ዋሻ ውስጥ ነቢዩ ሰ/ዐ/ወ/ ኸልዋ ወጥተው እያሉ ነው የወረደባቸው። (ቡኻሪና ሙስሊም፤ የወህይ አጀማመር ምእራፍ)
(2) 2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)::
(3) 3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው::
(4) 4. ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤
(5) 5. የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ)::
(6) 6. በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል::
(7) 7. ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት
(8) 8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::
(9) 9. ያንን የሚከለክለውን አየህን?
(10) 10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን):
(11) 11. እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤
(12) 12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን?
(13) 13. እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤
(14) 14. አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?
(15) 15. ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ አናቱን ይዘን አንጎትተዋለን::
(16) 16. ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን::
(17) 17. ሸንጎውንም ይጥራ፤
(18) 18. እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን::
(19) 19. በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ። {1}
{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ አለ። ይህ የመጨረሻ ሱጁድ ነው።