94 - Ash-Sharh ()
|
(1) 1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልብህን ላንተ አላሰፋንልህም?
(2) 2. ሸክምህንም አወረድንልህ?
(3) 3. ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)
(4) 4. መወሳትህንም ከፍ አላደረግንልህ?
(5) 5. እናም ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ::
(6) 6. ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ::
(7) 7. (የጀመርከውን ጥሩ ስራ) በጨረስክ ጊዜ ወደ ሌላ ጥሩ ስራ ቀጥል (አስከትል)።
(8) 8. ክጃሎትህንም ወደ ጌታህ ብቻ አድርግ።