81 - At-Takwir ()

|

(1) 1. ጸሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤

(2) 2. ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤

(3) 3. ተራራዎች በተናዱ ጊዜ፤

(4) 4. የአስር ወር እርጉዝ ግመሎች ያለጠባቂ በተተው ጊዜ፤

(5) 5. አራዊቶችም በተሰበሰቡ ጊዜ፤

(6) 6. ባህሮችም በተቀጣጠሉ ጊዜ፤

(7) 7. ነፍሶች በተቆራኙ ጊዜ፤

(8) 8. ከነሕይወቷ የተቀበረችው ሴት ልጅም በተጠየቀች ጊዜ፤

(9) 9. በምን ወንጀል እንደተገደለች፤ በተጠየቀች ጊዜ፤

(10) 10. ጹሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤

(11) 11. ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤

(12) 12. ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤

(13) 13 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤

(14) 14. ነፍስ (ሁሉ ከስራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤

(15) 15. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ተመላሾች በሆኑት (ከዋክብት) እምላለሁ::

(16) 16. አንዳንድ ጊዜ ሂያጆች በሌላ ጊዜ ገቢዎች በሆኑት

(17) 17. በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤

(18) 18. በንጋትም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ እምላለሁ::

(19) 19. እርሱ (ቁርኣን) የተከበረው መልዕክተኛ ጅብሪል ቃል ነው።

(20) 20. የኃይል ባለቤት የሆነ፤ ከዙፋኑ ባለቤት ዘንድም ባለሟል የሆነ፤

(21) 21. በዚያ ስፍራ ትዕዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝም የሆነው (መልዕክተኛ ቃል ነው)

(22) 22. ነብያችሁም በፍጹም እብድ አይደለም።

(23) 23. በግልጹ አድማስ ላይ ሆኖ (ጅብሪልን) በእርግጥ አይቶታል።

(24) 24. እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም::

(25) 25. (ቁርኣን) የርጉም ሰይጣን ቃልም አይደለም::

(26) 26. ታዲያ (ይህንን በተመለከተ) ወዴት ትሄዳላቸሁ?

(27) 27. እርሱ የዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::

(28) 28. ከናንተ መካከል ቀጥተኛ መሆንን ለፈለገ (ሁሉ መገሰጫ) ነው።

(29) 29. (ሰዎች ሆይ!) የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ካልሻ በስተቀር እናንተ አንድም ነገር አትሹም።