(1) 1. ተከታታይ ሆነው በተላኩት ፤ (እምላለሁ)፡፡
(2) 2. በኃይል መንፈስን ነፋሾች በሆኑትም (ንፋሶች)፤
(3) 3. መበተንን በታኝ በሆኑትም (ንፋሶች)፤
(4) 4. መለየትን ለይዎች በሆኑትም (መላዕክት)፤
(5) 5. መገሰጫን (ወደ ነብያት ጣይዎች) አምጪዎች በሆኑትም (መላዕክት)፤
(6) 6. ማሳበቢያን ለማስወገድ ወይም ለማስጠንቀቅ፤
(7) 7. ያ! የምትስፈራሩበት (ትንሳኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው ብየ እምላለሁ::
(8) 8. ከዋክብትም (ብርሃኗ) በታበሰች ጊዜ፤
(9) 9. ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፤
(10) 10. ጋራዎችም በተንኮታኮቱ ጊዜ::
(11) 11. መልዕክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፤
(12) 12. ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ የሚባል ሲሆን፤
(13) 13. ለዚያ ለመለያው ቀን ተቀጠሩ በተባለ ጊዜ (በፍጡሮች መካከል በትክክል ይፈርዳል)፤
(14) 14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመለያው ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
(15) 15. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።
(16) 16. የፊተኞቹን (ህዝቦች) አላጠፋንምን?
(17) 17. ከዚያ ኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን::
(18) 18. በአመጸኞች ሁሉ ላይ ልክ እንደዚሁ (ያለ) እንሰራለን።
(19) 19. ለአስተባባዩች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።
(20) 20. (ሰዎች ሆይ!) ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?
(21) 21. በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በእናቶች ማህጸን) ውስጥ አደረግነው::
(22) 22. እስከታወቀ ጊዜ ድረስ::
(23) 23.መጠንነዉም ምን ያማርንም መጣኞች ነን::
(24) 24. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።
(25) 25. (ሰዎች ሆይ!) ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን::
(26) 26. ህያው ሆናችሁም ሙታን ሆናችሁም።
(27) 27. በውስጧም ከፍተኛዎችን (ትላልቅ) ተራራዎች አደረግን፤ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ::
(28) 28. ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላችሁ::
(29) 29. «ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት ቅጣት ሂዱ።
(30) 30. ባለ ሶስት ቅርንጫፎች ወደ ሆነው ጥላ ሂዱ።» (ይባላሉም)
(31) 31. ጥላም ያልሆነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ሆነው (ሂዱ)::
(32) 32. እርሷ እንደ ታላላቅ ህንፃ የሆኑን ቃንቄዎች (የእሳት ፍንጣሪዎች) ትወረውራለች::
(33) 33. (ቃንቄዉም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል።
(34) 34. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
(35) 35. ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው።
(36) 36. ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ አይፈቀድላቸዉም::
(37) 37. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮውላቸው።
(38) 38. ይህ የመለያው ቀን ነው። እናንተንም የፊተኞችንም ሰበሰብናችሁ።
(39) 39. ለእናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ።
(40) 40. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
(41) 41. ጥንቅቆች በጥላዎችና በምንጮች፤ውስጥ ናቸው፡፡
(42) 42. በሚፈልጉትም የፍራፍሬ (አይነቶች) ውስጥ ናቸው።
(43) 43. «ትሰሩትም በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ሆናችሁ ብሉ፤ ጠጡም» ይባላሉ፤
(44) 44. እኛ መልካም ሰሪዎችን (ሁሉ) እንደዚሁ እንመነዳለን፤
(45) 45. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
(46) 46. አስትባባዮች ሆይ! ብሉ ጥቂትንም ጊዜ ተጠቀሙ እናንተ አመጸኞች ናችሁና::
(47) 47. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
(48) 48. ለእነርሱ «ስገዱ» በተባሉም ጊዜ አይሰግዱም።
(49) 49. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
(50) 50. ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?