91 - Ash-Shams ()

|

(1) 1. በጸሐይና በብርሀኗ፤ (እምላለሁ)

(2) 2. በጨረቃም ጸሐይን በተከተላት ጊዜ፤

(3) 3. በቀንም ጸሐይን በገለፃት ጊዜ፤

(4) 4. በሌሊቱም ጸሐይን በሸፈናት ጊዜ፤

(5) 5. በሰማይ እና በገነባትም፤

(6) 6. በምድር እና በዘረጋትም፤

(7) 7. በነፍስም ባስተካከላትም

(8) 8. አመጽዋንና ፍርሃቷንም ባሳወቃት (አምላክም በአላህ እምላለሁ)

(9) 9. (ነፍስን) ከኃጢአት ያጠራ ሰው ሁሉ በእርግጥ ተሳካለት።

(10) 10. በኃጢአትም የሸፈናት ሰው ሁሉ በእውነት አፈረ (ከሰረ)::

(11) 11. ሰሙድ ወሰን በማለፍዋ ምክንያት አስተባበለች፤

(12) 12. ጠማማዋ በተነሳ ጊዜ።

(13) 13. ለእነርሱም የአላህ መልዕክተኛ (ሷሊህ)፡-የአላህን ግመልና የመጠጥ ተራዋን (ጠብቁላት) አላቸው::

(14) 14. እነርሱ አስተባበሉትም፤ ከዚያ ወጓት፤ በኃጢአታቸዉም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም::

(15) 15. (የምታስተካክለውን) ፍፃሜዋንም አይፈራም።