109 - Al-Kaafiroon ()

|

(1) 1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)- (ለካሓዲያን እንዲህ) በላቸው፡- እናንተ ከሓዲያን ሆይ!

(2) 2.ያንን የምትገዙትን (ጣዖት አሁን) አልገዛም::

(3) 3.እናንተም እኔ የምገዛውን (አምላክ አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም::

(4) 4. እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደ ፊት) ተገዢ አይደለሁም::

(5) 5. እናንተም እኔ የምገዛውን (ወደ ፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም::

(6) 6. እናንተ የራሳችሁ ሃይማኖት አላችሁ:: እኔም የራሴ ሃይማኖት አለኝ -በላቸው::