(1) 1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ በዝሆኑ ባለቤቶች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወቅክምን?
(2) 2. ተንኮላቸውን በጥፋት ውስጥ ከንቱ አላደረገምን?
(3) 3. በእነርሱ ላይ መንጎች የሆኑን ወፎችንም ላከ።
(4) 4. ከተጠበሰ ጭቃ የሆነን ጠጠር የምትወረውርባቸውን የሆነችን (አእዋፍ)
(5) 5. እና ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራ አደረጋቸው