(1) 1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል፡ -የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሆነው ጌታ እጠበቃለሁ፤
(2) 2.የሰዎች ሁሉ ንጉስ በሆነው ጌታ፤
(3) 3.የሰዎች ሁሉ አምላክ በሆነው ጌታ፤
(4) 4. ከዚያ ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች ክፋት፤
(5) 5. ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከሆነው፤
(6) 6. ከጂንም ይሁን ከሰው ሰይጣን ክፋት (እጠበቃለሁ)።