41 - Fussilat ()

|

(1) 1. ሓ፤ ሚይም፤

(2) 2. ይህ ቁርኣን እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ከሆነው ጌታ ከአላህ የተወረደ ነው::

(3) 3. አናቅጾቹ የተብራሩ የሆነ መጽሐፍ ነው:: ዐረበኛ ቁርኣን ሲሆን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው::

(4) 4. አብሳሪና አስፈራሪ ሲሆን ተወረደ። አብዛኞቻቸዉም ተውት:: እነርሱም አይሰሙም::

(5) 5. አሉም፡- «ልቦቻችን ከዚያ ወደርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው:: በጆሮቻችንም ላይ ድንቁርና አለ:: በእኛና በአንተ መካከል ግርዶሽ አለ:: በሃይማኖትህ ስራ እኛም ሰሪዎች ነንና::»

(6) 6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ቀጥ በሉ:: ምህረትንም ለምኑት በማለት ወደ እኔ ይወርድልኛል እንጂ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ።» ለአጋሪዎችም ወዮላቸው።

(7) 7. ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲያን ለሆኑት (ወዮላቸው)::

(8) 8. እነዚያ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው::

(9) 9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !) «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባላንጣዎች ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሰራው) የዓለማቱ ጌታ ነው።» በላቸው::

(10) 10. በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ:: በእርሷም በረከትን አደረገ:: በውስጧም ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆን ወሰነ::

(11) 11. ከዚያም እርሷ ጭስ ሆና ሳለች ወደ ሰማይ አሰበ:: ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ኑ» አላቸው:: «ታዛዦች ሆነን መጣን» አሉ::

(12) 12. በሁለት ቀናትም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: በሰማያትም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ:: ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን:: ከሰይጣናት መጠበቅንም ጠበቅናት:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው ጌታ ውሳኔ ነው::

(13) 13. ከእምነት እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የሆነን መቅሰፍት አስጠነቅቄያችኋለሁ።»

(14) 14. መልዕክተኞቹ «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ» በማለት ከስተፊታቸዉም ከበስተኋላቸዉም በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላዕክትን ባወረደ ነበር:: ስለዚህ እኛ በዚህ በእርሱ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» አሉ።

(15) 15. የዓድም ነገዶችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፤ ከእኛ ይበልጥ በኃይል ብርቱ ማን ነው ? አሉም ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኃይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መሆኑን አያምኑምን? በታዐምራታችንም ይክዱ ነበሩ::

(16) 16. በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸዉም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻ ብርቱ ነፋስ መናጢዎች በሆኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው:: እነርሱም አይረዱም::

(17) 17. ሰሙዶችማ ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: እነርሱ ግን እውርነትን ከቅንነት ይልቅ መረጡ:: ይሰሩትም በነበሩት ኃጢአት አዋራጅ የሆነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው::

(18) 18. እነዚያንም ያመኑትንና ይጠነቀቁ የነበሩትንም አዳንናቸው::

(19) 19. የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውሱ:: የሚከመከሙ ሆነውም ይነዳሉ።

(20) 20. በመጧትም ጊዜ ጀሮዎቻቸው፤ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸዉም ይሰሩት በነበረ ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል::

(21) 21. ለቆዳዎቻቸዉም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ። «ያ ሁሉን ነገር ያናገረው አላህ አናገረን:: እርሱም (ነው) በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ። ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል::

(22) 22. ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁ በእናንተ ላይ እንዳይመሰክሩባችሁ የምትደበቁባቸው አልነበራችሁም:: ግን አላህ ከምትሰሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ::

(23) 23. ይህም ለጌታችሁ የጠረጣችሁት ጥርጣሬያችሁ አጠፋችሁ:: ከከሳሪዎችም ሆናችሁ ይባላሉ::

(24) 24. ቢታገሱም እሳት ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት:: ወደ ሚወዱት መመለስንም ቢጠይቁ እነርሱ ተቀባይ የሚያገኙ አይደሉም::

(25) 25. ለእነርሱም ቁራኛዎችን አዘጋጀንላቸው:: በፊታቸውን ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ለእነርሱ ሸለሙላቸው:: ከአጋንንትና ከሰዉም ከእነርሱ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆነው ቃሉ በእነርሱ ላይ ተረጋገጠባቸው:: እነርሱ በእርግጥ ከሳሪዎች ነበሩና::

(26) 26. እነዚያም «በአላህ የካዱት ሰዎች ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብም ተንጫጩበት።» አሉ።

(27) 27. እነዚያንም በአላህ የካዱትን ብርቱ ቅጣት እናቀምሳቸዋለን:: የእነዚያንም ይሰሩት የነበሩትን መጥፎውን ፍዳ እንመነዳቸዋለን::

(28) 28. ይህ የአላህ ጠላቶች ፍዳ እሳት ነው:: በውስጧም ለእነርሱ የዘላለም መኖሪያ አገር አላቸው:: በአንቀፆቻቸን ይክዱ በነበሩት ምንዳ ይመነዳሉ::

(29) 29. እነዚያም በአላህ የካዱት በእሳት ውስጥ ሆነው «ጌታችን ሆይ! እነዚያ ከአጋንንትና ከሰው ያሳሳቱንን አሳየን። ከታችኞች ይሆኑ ዘንድ ከጫማዎቻችን ስር እናደርጋቸዋለንና» ይላሉ::

(30) 30. እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም ቀጥ ያሉ። እንዲህ እያሉ መላዕክቱ በነርሱ ላይ ይወርዳሉ: «አትፍሩ አትዘኑ:: በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላቸሁ:: በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ።

(31) 31. «እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ:: ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምታዙት ሁሉ አለላችሁ::

(32) 32. «መሀሪና አዛኝ ከሆነው አላህ መስተንግዶ ሲሆን» ይባላሉ።

(33) 33. ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

(34) 34. መልካሚቱና ክፉይቱም ጸባይ አይስተካሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፤ ያን ጊዜ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ ወዳጅ ዘመድ ይሆናል::

(35) 35. ይህችንም ጸባይ እነዚያን የታገሱት እንጂ ሌላው አያገኛትም:: የትልቅም እድል ባለቤት እንጂ ማንም አያገኛትም::

(36) 36. ከሰይጣን ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጸባይ ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::

(37) 37. ሌሊትና ቀንም ጸሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለጸሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ:: እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)::

(38) 38. ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ:: እነርሱም አይሰለቹም:: {1}
{1} እዚህ የቲላዋ ሱጁድ ይደረጋል።

(39) 39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ በቡቃያዎችዋ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም። ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንንም ህያው አድራጊ ነው:: እርሱ በነገሩ ሁሉ ቻይ ነውና።

(40) 40. እነዚያ አናቅጻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም:: (የሚያጣምም) በእሳት ውስጥ የሚጣለው ይበልጣልን? ወይስ በትንሳኤ ቀን ደህነኛ ሆኖ የሚመጣው? የሻችሁትን ስሩ:: ዋጋችሁን ታገላችሁ:: እርሱም (አላህ) የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::

(41) 41. እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊው መጽሐፍ ሲሆን በመጣላቸው ጊዜ የካዱ ሁሉ ጠፊዎች ናቸው::

(42) 42. ከኋላዉም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም:: ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው::

(43) 43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት መልዕክተኞች የተባለው ቢጤ እንጂ ላንተ ሌላ አይባልም:: ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣትም ባለቤት ነው::

(44) 44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአዕጀምኛ የሆነ ቁርኣን ባረግነው ኖሮ «አናቅጹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አዕጀምኛና (መልዕክተኛው) አረባዊ ይሆናልን?» ባሉ ነበር:: እርሱ ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎች መመሪያና መፈወሻ ነው:: እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው (አይሰሙትም):: እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው:: እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው::

(45) 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፤ እነርሱም በእርሱ አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::

(46) 46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካምን የሰራ ለነፍሱ ነው:: ያጠፋም በእርሷው ላይ ነው:: ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም::

(47) 47. የትንሳኤ መከሰቻ ሰዐቱን ማወቅ ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፤ አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ:: «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም ከእኛ ውስጥ («ተጋሪ አለህ» ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አምነናል» ይላሉ::

(48) 48. ያም በፊት ይገዙት የነበሩት ጣዖት ከእነርሱ ይጠፋቸዋል:: ለእነርሱም ምንም መሸሻ የሌላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ::

(49) 49. ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም:: ክፋት ቢያገኘው (ግን) ወዲያውኑ በጣም ተስፋ ቆራጭ ተበሳጭ ይሆናል::

(50) 50. ካገኘችዉም መከራ በኋላ ከእኛ የሆነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ በስራየ የተገባኝ ነው፤ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብየ አላስብም። ወደ ጌታየ ብመለስ (እንኳ) ለእኔ እርሱ ዘንድ መልካሚቱ ገነት በእርግጥ አለችኝ» ይላል:: እነዚህም የካዱትን ስራዎቻቸውን በእርግጥ እንነግራቸዋለን:: ከበረታዉም ስቃይም በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::

(51) 51. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከማመስገን ይዞራል በጎኑም ይርቃል:: መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይሆናል::

(52) 52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «እስቲ ንገሩኝ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ ቢሆንና ከዚያም በእርሱ ብትክዱ፤ ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከሆነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»

(53) 53. እርሱም (ቁርኣን) እውነት መሆኑ ለእነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ በአጽናፎችና በነፍሶቻቸዉም ውስጥ ያሉትን ታዐምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን:: ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸዉምን?

(54) 54. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እነርሱ ከጌታቸው ጋር መገናኘትን በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ በነገሩ ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነው::