102 - At-Takaathur ()

|

(1) 1. (በዚህች ዓለም ጸጋዎች) ብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘናጋችሁ::

(2) 2. መቃብሮችን እስከጎበኛችሁ ድረስ:: (በዚሁ ላይ ቀጠላችሁ)

(3) 3. ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ (ታቀቡ):: ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፤

(4) 4. ከዚያም ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ። ወደ ፊትም ታውቃላችሁ፤

(5) 5. በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) በእርግጠኝነት ብታውቁ ኖሮ (ይህን ያክል ባልተዘናጋችሁ ነበር)

(6) 6. ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ::

(7) 7. ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፤

(8) 8. ከዚያም በድሎታችሁ ጉዳይ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃለችሁ::