(1) 1. የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤
(2) 2. በተቀጠረዉም ቀን፤
(3) 3. በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ::
(4) 4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ::
(5) 5. የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች።
(6) 6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)።
(7) 7. እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው።
(8) 8. ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ ጌታ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም::
(9) 9. ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)።
(10) 10. እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው:: ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው::
(11) 11. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው:: ይህ ታላቅ ስኬት ነው::
(12) 12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው።
(13) 13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም::
(14) 14. እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው::
(15) 15. የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው።
(16) 16. የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው::
(17) 17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን?
(18) 18. የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)?
(19) 19. በእውነት እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው::
(20) 20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው::
(21) 21. ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::
(22) 22. የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው::