89 - Al-Fajr ()

|

(1) 1. በጎህ፤ እምላለሁ

(2) 2. በአስሩ ሌሊቶችም፤

(3) 3. በጥንዱም በነጠላዉም፤

(4) 4. በሌሊቱም በሚጓዝበት ጊዜ እምላለሁ።

(5) 5. በዚህ መሀላ ለባለ አእምሮ ታላቅ መሀላ የለበትምን?

(6) 6. ጌታህ በዓድ ህዝቦች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወክምን?

(7) 7. በባለ ረዣዥሚቱ አዕማድ ኢረም ላይም፤

(8) 8. በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በሆነችው፤

(9) 9. በእነዚያ (በሸለቆዎች) ቋጥኝን የቦረቦሩ በሆኑት ሰሙድም፤

(10) 10. ባለ ችካሎች በሆነው ፈርዖንም፤

(11) 11. በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሰሩ (በሆኑትም ላይ)

(12) 12. በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሰራ አታውቅምን?)

(13) 13. በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው::

(14) 14. ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና::

(15) 15. የሰው ልጅ ጌታው በሞከረው ጊዜ ባከበረውና ባጣቀመው ጊዜ ጌታየ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል::

(16) 16. በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበበት (ጊዜ) እንዲሁ ጌታየ አሳነሰኝ ይላል::

(17) 17. በፍፁም! ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤

(18) 18. ድሃንም በማብላት ላይ አትበረታቱም፤

(19) 19. የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል (ያለአግባብ) ትበላላችሁ፤

(20) 20. ገንዘብንም አብዝታችሁ (አለቅጥ) ትወዳላችሁ፤

(21) 21. (ሰዎች ሆይ! ተዉ):: ታቀቡ:: ምድር ደጋግማ በተንኮታኮተች ጊዜ፤

(22) 22. ጌታህ በመጣና መላዕክትም በሰልፍ በሰልፍ ሆነው በመጡ ጊዜ፤

(23) 23. ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው ሁሉ ጥፋቱን በትክክል ይገነዘባል። መገንዘቡ በየት በኩል (ይጥቀመው)?

(24) 24. "ወይ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ስራ) ባስቀደምኩ ኖሮ" ይላል።

(25) 25. በዚያ ቀንም የእርሱን አቀጣጥ የመሰለ አንድም አካል አይቀጣም።

(26) 26. የእርሱንም፤አሰተሳሰር አንድም አካል አያስርም::

(27) 27. (ለአመነች ነፍስም እንዲህ ትባላለች)፡- አንቺ በአላህ የረካሺው ነፍስ ሆይ!

(28) 28. (ከእርሱም) የወደድሽ፤ (እርሱ ዘንድም) የተወደደሽ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ::

(29) 29. ከዉድ ባሮቼም ጋር ተቀላቀይ::

(30) 30. ወደ ገነቴም ግቢ ትባላለች::