(1) 1. ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤
(2) 2. የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
(3) 3. ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
(4) 4. በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በሆነች ጊዜ፤
(5) 5. ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (ልትስማ) ተገባትም፤
(6) 6. አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን በሞት እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ። ተገናኚዉም ነህ።
(7) 7. ያ! መጽሐፉን በቀኝ እጅ የተሰጠውማ
(8) 8. በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል።
(9) 9. ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ሆኖ (በደስታ) ይመለሳል::
(10) 10. ያ ! መጽሐፉን በጀርባው በኩል የተሰጠው ግን
(11) 11. (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል::
(12) 12. የተጋጋመች እሳትንም ይገባል::
(13) 13. እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፤
(14) 14. እርሱም ወደ አላህ እንደማይመለስ አሰበ።
(15) 15. አይደለም (ይመለሳል)፤ ጌታው በእርሱ (መመለስ) አዋቂ ነው።
(16) 16. ስለሆነም በወጋገኑ እምላለሁ።
(17) 17. በሌሊቱና በሰበሰበዉም ሁሉ፤
(18) 18. በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)።
(19) 19. ከአንድ እርከን ወደ ሌላ እርከን ትሸጋገራላችሁ።
(20) 20. የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው ( ምን ሆነው ነው)?
(21) 21. በእነርሱ ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱትስ ለእነርሱ ምን አላቸውና ነው?
(22) 22. በእርግጥ እነዚያ የካዱት ያስተባብላሉ።
(23) 23. አላህ በልቦቻቸው የሚቋጥሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::
(24) 24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።
(25) 25.እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ተግባራትን የሰሩት ሲቀሩ፤ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው።