(1) 1. መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ
(2) 2. ከባድ ዝናብን ተሸካሚዎች በሆኑትም (ዳመናዎች)፤
(3) 3. ገር መንሻለልን ተንሻላዩች በሆኑትም (መርከቦች) እምላለሁ::
(4) 4. ጉዳይን ሁሉ አከፋፋዮች በሆኑትም (መላዕክት) እምላለሁ::
(5) 5. የምተቀጠሩት ትንሳኤ እውነት ነው::
(6) 6. (እንደየስራው) ዋጋን ማግኘትም የማይቀር ነው።
(7) 7.የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::
(8) 8. እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ።
(9) 9. ከእርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል::
(10) 10. በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ::
(11) 11. እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት::
(12) 12. የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ::
(13) 13. (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው::
(14) 14. «መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::
(15) 15. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
(16) 16. ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው በገነት ውስጥ ይሆናሉ:: እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና::
(17) 17. ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር::
(18) 18. በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ::
(19) 19. በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ።
(20) 20. በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ::
(21) 21. (ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ:: ታዲያ አትመለከቱምን?
(22) 22. ሲሳያችሁም የምትቀጠሩት (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው።
(23) 23. በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው።
(24) 24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?
(25) 25. በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው።
(26) 26. ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ::
(27) 27. ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ? አላቸው።
(28) 28. ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት::
(29) 29. ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም።
(30) 30. እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት::
(31) 31. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው::
(32) 32. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ አመጸኖች ህዝቦች ተልከናል።
(33) 33. «በእነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑ ድንጋዮችን ልንለቅባቸው ተላክን።
(34) 34. «በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ በየስማቸው ምልክት የተደረገባት ስትሆን።» አሉ
(35) 35. ከምዕመናም በእርሷ በከተማቸው ውስጥ የነበሩትን አወጣን::
(36) 36. በውስጧም ከአንድ ቤት ቤተሰቦች በስተቀር ሙስሊሞችን አላገኘንም::
(37) 37. በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን::
(38) 38. በሙሳ ወሬ ውስጥም ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)::
(39) 39. ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም ከእምነት ዞረ:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» አለ::
(40) 40. እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባህር ውስጥ ጣልናቸውም።
(41) 41. በዓድም በእነርሱ ላይ መካን (የሆነች) ንፋስን በላክን ጊዜ ምልክት አለ::
(42) 42. በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛዉንም ነገር እንደበሰበሰ አጥነት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወዉም።
(43) 43. በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ።» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)።
(44) 44. ከጌታቸው ትዕዘዝም ኮሩ:: እነርሱም እያዩ ጩኸቷ ያዘቻቸው::
(45) 45. መቆምንም አልቻሉም:: እርዳታ የሚደረግላቸውም አልነበሩም::
(46) 46. የኑህንም ህዝቦች (ከዚህ በፊት አጠፋን) እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::
(47) 47. ሰማይንም በሀይል ገነባናት:: እኛም በእርግጥ የምናስፋት ነን::
(48) 48. ምድርንም ዘረጋናት ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን::
(49) 49. ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ አይነትን ፈጠርን::
(50) 50. ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ።
(51) 51. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላኩ:: ግልጽ አስፈራሪ ነኝና::
(52) 52. ልክ እንደዚሁ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልዕክተኛ ማንም አልመጣቸዉም:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» ያሉ ቢሆን እንጂ::
(53) 53. በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? ይልቁን እነርሱ ጥጋበኞች ህዝቦች ናቸው::
(54) 54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ዘወር በል (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና::
(55) 55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና::
(56) 56. ጋኔንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::
(57) 57. ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም:: እንዲመግቡኝም አልፈልግም::
(58) 58. አላህ ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና::
(59) 59. ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ የቅጣት ፋንታ አለላቸው:: ስለዚህ አያስቸኩሉኝ::
(60) 60. ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዩላቸው::