69 - Al-Haaqqa ()

|

(1) 1. እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሳኤ)::

(2) 2. አረጋጋጪቱ (እርሷ) ምንድን ናት!

(3) 3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አረጋግጪቱም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

(4) 4. የሰሙድና የዓድ ህዝቦች በቆርቋሪይቱ (ትንሳኤ) ቀን አስተባበሉ::

(5) 5. የሰሙድ ህዝቦችማ ወሰን በሌላት ነፋስ ጩኸት ተጠፉ::

(6) 6. የዓድ ህዝቦችማ በኃይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ::

(7) 7. ተከታታይ በሆነ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት ቀናቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት:: ህዝቦችንም፤ በውስጧ የተጣሉ ሆነው ልክ ክፍት እደሆኑ የበሰበሱ የዘንባባ ግንዶች ታያቸዋለህ::

(8) 8. ከእነርሱ መካከል ቀሪን ታያለህን?

(9) 9. ፈርዖን፤ ከበፊቱ የነበሩትን ሰዎችም፤ ተገልባጮችም (የሉጥ ሰዎች ከተሞች) ኃጢአት ፈጸሙ።

(10) 10. የጌታቸውንም መልዕክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፤ የበረታችንም ቅጣት ቀጣቸው::

(11) 11. እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሳፋፊይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ::

(12) 12. ይህንም ያደረግነው ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋትና አጥኚ የሆነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ ነው::

(13) 13. በቀንዱ አንዲት መነፋት በተነፋች ጊዜ::

(14) 14. ምድርና ጋራዎች (ከየስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፤

(15) 15. በዚያ ቀን (ትንሳኤ) ትከሰታለች::

(16) 16. ሰማይም ትቀደዳለች:: በመሆኑም እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፤

(17) 17. መላዕክትም በየጫፎቿ ላይ ይሆናሉ:: የጌታህንም ዓርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላዕክት ከበላያቸው ይሸከማሉ::

(18) 18. በዚያ ቀን ከናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲሆኑ ትቀረባላችሁ::

(19) 19. ያ መጽሀፉን በቀኝ እጁ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ እንዲህ) ይላል: «እንኩ መጽሐፌን አንብቡ፤

(20) 20. «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መሆኔን አረጋገጥኩ።» (ይላል)

(21) 21. እርሱም በተወደደች ኑሮ ውስጥ ይሆናል::

(22) 22. በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፤

(23) 23. ፍሬዎቿ ቅርቦች የሆኑ::

(24) 24. በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም ይባላሉ::

(25) 25. ያ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ደግሞ (እንዲህ) ይላል: «ዋ ጥፋቴ ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ፤

(26) 26. «ምርመራዬም ምን እንደሆነ ባላወቅሁ፤

(27) 27. «ሞት ምነው የህይወቴ የመጨረሻ ፍፃሜ በሆነች፤

(28) 28. «ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አልጠቀመኝም፤

(29) 29. «ስልጣኔ ከእኔ ላይ ጠፋ» ይላል::

(30) 30. ያዙት ከዚያ እጁን ከአንገቱ ጋር እሰሩት፤

(31) 31. ከዚያ በእሳት ውስጥ አስገቡት፤

(32) 32. ከዚም እርዝመቷ ሰባ ክንድ በሆነች ሰንሰለት ውስጥ አስገቡት።

(33) 33. እርሱ ታላቅ በሆነው አላህ አያምንም ነበርና፤

(34) 34. ድሆችንም በማብላት ላይ አያነሳሳም ነበርና::

(35) 35. ለእርሱ ዛሬ እዚህ ቦታ ዘመድ ማንም የለዉም::

(36) 36. ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ እዥ በስተቀር የለዉም::

(37) 37. ይህን ምግብ ኃጢአተኞች እንጂ ሌላ አይበላዉም ይባላል::

(38) 38. በምታዩት ነገር ሁሉ እምላለሁ ::

(39) 39. በማታዩትም ነገር ሁሉ እምላለሁ ::

(40) 40. ቁርኣን የተከበረው መልዕክተኛ ቃል ነው።

(41) 41. እርሱም የባለ ቅኔ ገጣሚ ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ::

(42) 42. የጠንቋይም ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ::

(43) 43. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::

(44) 44. በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት እንኳን (ያላልነው) በቀጠፈ ኖሮ፤

(45) 45. በኃይል በቀጣነው ነበር::

(46) 46. ከዚያ ከእርሱ የልቡን ስር የተንጠላጠለበትን (ጅማት) በቆረጥን ነበር::

(47) 47. ከናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም።

(48) 48. እርሱ (ቁርኣን) ለጥንቅቆቹ ብቻ መገሰጫ ነው::

(49) 49. እኛም ከናንተ ውስጥ አስተባባዩች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን::

(50) 50. እርሱ (ቁርኣንም) በከሓዲያን ላይ ጸጸት ነው::

(51) 51. እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው::

(52) 52. እናም የታላቁን ጌታህን ስም (ታላቁን ጌታህን) አጥራው::