71 - Nooh ()

|

(1) 1. እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው::

(2) 2. እርሱም አለ፡- «ሀዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) ገላጭ የሆንኩ አስጠንቃቂ ነኝ::

(3) 3. «አላህን ተገዙት፡-ፍሩት፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ።

(4) 4. «ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል:: አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይቆይም:: በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ በታዘዛችሁ ነበር።»

(5) 5. ስለተቃወሙትም «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ።

(6) 6. «ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።

(7) 7. «እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ:: ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ:: በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም:: ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ::

(8) 8. «ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው።

(9) 9. «ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ:: ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ።

(10) 10. «እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: እርሱም በጣም መሀሪ ነውና።

(11) 11. «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል።

(12) 12. «ገንዘቦችና ልጆችንም ይለግሳችኋል:: ለእናንተ አትክልቶችን ያደርግላችኋል:: ለእናተም ወንዞችን ያደርግላችኋል አልኳቸው።»

(13) 13. ለአላህ ተገቢውን ልቅና የማትሰጡበት ምክንያት ለእናንተ ምን አላችሁ?

(14) 14. በልዩ ልዩ (በተለያዩ) እርከኖች (ሁኔታዎች) በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲሆን::

(15) 15. አላህ ሰባት ሰማያትን አንዱ በአንዱ ላይ የተነባበረ ሲሆን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?

(16) 16. በውስጣቸዉም ጨረቃን አብሪ አደረገ:: ጸሐይንም ብርሃን አደረገ::

(17) 17. አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ::

(18) 18. ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል:: ማውጣትንም ያወጣችኋል::

(19) 19. አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት።

(20) 20. ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ::

(21) 21. ኑሕም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! እነርሱም አመጹብኝ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ።

(22) 22. «ከባድንም ተንኮል ያሴሩትን ሰዎች ተከተሉ።

(23) 23. መሪዎችም አሉ፡- <አማልክቶቻችሁን፤ ወድንም፤ ሰዋዕንም፤ የጉስንም፤ የዑቅንና ነስርንም አትተው።>

(24) 24. «በእርግጥ (እነዚህ መሪዎች ወይም ጣኦቶች) ብዙዎችን ሰዎች አሳሳቱ:: ከሓዲያንንም ጥመትን እንጂ ሌላን አትጨምርላቸው» አለ።

(25) 25. በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ተሰመጡ:: እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ:: ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሆኑ ረዳቶችን አላገኙም::

(26) 26. ኑህም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ከከሓዲያን በምድር ላይ (በዓለም ላይ) የሚኖርን አንድንም አትተው።

(27) 27. «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና:: ኃጢአተኛ ከሓዲንም እንጂ ሌላን አይወልዱም።

(28) 28. «ጌታየ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ትክክለኛ አማኝ ሆኖ በቤቴ ለገባ ሁሉ ለአማኞችና ለምዕመናትም ምህረት አድርግ:: ከሓዲያንንም ከጥፋት በስተቀር አትጨምርላቸው።» አለ።