(1) 1. በጊዜ እምላለሁ፤
(2) 2. ሰው ሁሉ በእርግጥ በኪሳራ ውስጥ ነው::
(3) 3. እነዚያ በአላህ በትክክል ያመኑትና መልካሞችን የሰሩ፤ በእውነትም ላይ አደራ የተባባሉ፤ በመታገስም ላይ አደራ የተባባሉ ብቻ ሲቀሩ::