76 - Al-Insaan ()

|

(1) 1. በሰው ላይ የሚታወስ ነገር (እንኳ) ሳይሆን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ አላለፈም ነበርን? (በእርግጥ አልፏል)

(2) 2. እኛ ሰውን (በሕግጋት ግዳጅ) የምንሞክረው ስንሆን ከወንድና ከሴት ፈሳሽ ቅልቅሎች ከሆነች የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው:: ሰሚና ተመልካችም አደረግነው።

(3) 3. እኛ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲሆን መንገዱን መራነው::

(4) 4. እኛ ለከሓዲያን ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም (አዘጋጅተናል)::

(5) 5. እነዚያ (ትክክለኛ) በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ::

(6) 6. ከእርሷ እነዚያ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት ና ወደ ፈለጉበት ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከሆነች የጠጅ ምንጭ (ይጠጣሉ)::

(7) 7. (ዛሬ በዚህ ዓለም እያሉ) በስለታቸው ይሞላሉ:: መከራው ተሰራጪ የሆነንም ቀን ይፈራሉ::

(8) 8. ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድሃ፤ ለየቲምና ለምርኮኛ ያበላሉ::

(9) 9. «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው:: ከናንተ ክፍያንም ሆነ ማመስገንን አንፈልግም::

(10) 10. እኛ ያንን (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» (ይላሉ)

(11) 11. አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው። (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው::

(12) 12. በመታገሳቸዉም (ምክንያት) ገነትንና የሀር ልብስን መነዳቸው::

(13) 13. በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች፤ በውስጧ የጸሀይን ሐሩርንም ሆነ ብርድንም የማያዩ ሲሆኑ፤

(14) 14. ዛፎቿም ለእነርሱ የቀረበች፤ ፍራፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መገራትን የተገራች ስትሆን ገነትን መነዳቸው::

(15) 15. በእነርሱም ላይ ከብር በተሰሩ ዕቃዎች (ሳህኖች)፤ ብርጭቆዎች እና በኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል::

(16) 16. መለካትን የለኳቸው በሆኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)::

(17) 17. በእርሷም መበረዣዋ ዝንጂብል የሆነች ወይን ጠጅ ይጥጠጣሉ።

(18) 18. በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ::

(19) 19. በእነርሱም ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ:: ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ::

(20) 20. እዚያንም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግስናን ታያለህ::

(21) 21. አረንጓዴዎች የሆኑ ቀጭን ሀር ልብሶችና ወፍራም ሀርም በላያቸው ላይ አለ። ከብር የሆኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ:: ጌታቸዉም (ከራሱ አልፎ) ሌላን አጥሪ የሆነን መጠጥ ያጠጣቸዋል::

(22) 22. «ይህ ለእናንተ ዋጋ ሆነ:: ስራችሁም ምስጉን ሆነ» ይባላሉ::

(23) 23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ (ይህንን) ቁርኣን ባንተ ላይ ማውረድን አወረድነው።

(24) 24. ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: ከእነርሱም መካከል ኃጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ::

(25) 25. የጌታህን ስም በጠዋትና ከቀትር በኋላ አውሳ::

(26) 26 ከሌሊቱም ለእርሱ ብቻ ስገድ፤ በረዢም ሌሊትም አወድሰው።

(27) 27. እነዚያ ይህችን ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ። ከባድና (አስቸጋሪ) ቀንም በስተፊታቸው ሆኖ ችላ ይላሉ::

(28) 28. እኛ ፈጠርናቸው:: የአካሎቻቸዉንም መለያያቸውን አጠነከርን:: በፈለግን ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን።

(29) 29. ይህ መገሰጫ ነው:: የፈለገ ሰውም ወደ ጌታው መንገድ ይይዛል::

(30) 30. አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፤ አላህ አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

(31) 31. (አላህ) የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዩችንም (ዝቶባቸዋል) ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል::