97 - Al-Qadr ()

|

(1) 1. እኛ (ቁርኣንን) በመወሰኛይቱ ሌሊት ውስጥ አወረድነው።

(2) 2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

(3) 3. የመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር የምትበልጥ ነች።

(4) 4. በእርሷ ውስጥ መላዕክትና ሩሕም (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በሁሉም ጉዳዮች ይዘው ይወርዳሉ።

(5) 5. እርሷም ጎህ እስኪወጣ ድረስ ሰላም ነች።