(1) 1. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
(2) 2. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት) ምንድን ናት!
(3) 3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቆርቋሪይቱ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
(4) 4. ሰዎች እንደተበታተነ ቢራቢሮ (ኩብኩባ) የሚሆኑበት ቀን፤
(5) 5. ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ የሚሆኑበት (አስደንጋጭ ቀን) ናት።
(6) 6. በዚያ ዕለት ያ ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ
(7) 7. እርሱ ኑሮው በአሰደሳቿ ጀነት ውስጥ ይሆናል።
(8) 8. ያ ሚዛኖቹ የቀለሉበት ሰው ደግሞ
(9) 9. መኖሪያው ሃዊያህ (የምትባል የገሀነም እሳት) ናት።
(10) 10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሷ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
(11) 11. (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት::